ምዕራፍ 126
1እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።
2በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።
3እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።
4አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።
5በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ።
6በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ።