ምዕራፍ 10
1ያተሙትም እነዚህ ናቸው፤ የሐካልያ ልጅ ሐቴርሰታ ነህምያ፥
2ሴዴቅያስ፥ ሠራያ፥
3ዓዛርያስ፥ ኤርምያስ፥ ፋስኮር፥ አማርያ፥ መልክያ፥
4
5ሐጡስ፥ ሰበንያ፥ መሉክ፥ ካሪም፥
6ሜሪሞት፥ አብድዩ፥ ዳንኤል፥ ጌንቶን፥ ባሮክ፥
7
8ሜሱላም፥ አብያ፥ ሚያሚን፥ መዓዝያ፥ ቤልጋል፥ ሸማያ፤ እነዚህ ካህናት ነበሩ።
9ሌዋውያኑም፤ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኤንሐዳድ ልጆች ቢንዊ፥ ቀድምኤል፤
10ወንድሞቻቸውም ሰባንያ፥ ሆዲያ፥ ቆሊጣስ፥
11ፌልያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረአብ፥ ሐሸብያ፥
12
13ዘኩር፥ ሰራብያ፥ ሰበንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒ፥ ብኒኑ።
14የሕዝቡ አለቆች፤ ፋሮስ፥ ፈሐት ሞዓብ፥
15ኤላም፥ ዛቱዕ፥ ባኒ፥ ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥
16
17አዶንያስ፥ በጉዋይ፥ ዓዲን፥ አጤር፥ ሕዝቅያስ፥
18ዓዙር፥ ሆዲያ፥ ሐሱም፥ ቤሳይ፥
19
20ሐሪፍ፥ ዓናቶት፥ ኖባይ፥ መግጲዓስ፥ ሜሱላም
21
22ኤዚር፥ ሜሴዜቤል፥ ሳዶቅ፥ ያዱአ፥ ፈላጥያ፥
23ሐናን፥ ዓናያ፥ ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ አሱብ፥
24
25አሎኤስ፥ ፈልሃ፥ ሶቤቅ፥ ሬሁም፥ ሐሰብና፥
26
27መዕሤያ፥ አኪያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥ መሉክ፥ ካሪም፥ በዓና።
28የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወደ ወንድሞቻቸው ወደ ታላላቆቻቸው ተጠጉ፤
29በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የጌታችንንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ፍርዱንም ሥርዓቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እርግማንና መሐላውን አደረጉ።
30ሴቶች ልጆቻችንንም ለምድር አሕዛብ አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችን አንወስድም፤
31የምድርን አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ የሰባተኛውንም ዓመት ፍሬና ዕዳን ማስከፈል እንተዋለን ብለው ማሉ።
32
33ስለ አምላካችንም ቤት አገልግሎት፥ ስለ ገጸ ኅብስትም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቍርባንና ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት፥ ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ትእዛዝ በራሳችን ላይ አደረግን።
34እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቍርባን ዕጣ ተጣጣልን፤
35በየዓመቱም የመሬታችንን በኵራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኵራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
36በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
37የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቍርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
38ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።
39የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣት ቍርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፤ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።