English

ምዕራፍ 130

1አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።
2አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፤ ጆሮህ የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይሁን።
3አቤቱ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል?
4ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና።
5አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሠች።
6ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች።
7ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን ነውና እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን።
8እርሱም እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።