English

ምዕራፍ 150

1ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት።
2በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።
3በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።
4በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት።
5ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።
6እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።