English

ምዕራፍ 66

1በምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥
2ለስሙም ዘምሩ፥ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ።
3እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት። ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።
4በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ።
5ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፤ ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር ግሩም ነው።
6ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፤ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።
7በኃይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ ዓይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፤ ዓመፀኞች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።
8አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን ባርኩ፥ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
9ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥ እግሮቼንም ለመናወጥ አልሰጠም።
10አቤቱ፥ ፈትነኸናልና፥ ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና።
11ወደ ወጥመድ አገባኸን፥ በጀርባችንም መከራን አኖርህ።
12በራሳችን ላይ ሰውን አስረገጥኸን፤ በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን፥ ወደ ዕረፍትም አወጣኸን።
13-
14ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን ከንፈሮቼም ያሉትን ስእለቴን ለአንተ እፈጽማለሁ።
15ከዕጣንና ከወጠጤዎች ጋር ለሚቃጠል መሥዋዕት ፍሪዳን አቀርባለሁ፤ ላሞችንና ፍየሎችን እሠዋልሃለሁ።
16እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።
17በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፥ በአንደበቴም አመሰገንሁት።
18በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።
19ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፤ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ።
20ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።