ምዕራፍ 8
1ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥
2ሦስተኛውንም አሐራን፥ አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ።
3ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ አዳር፥
4ጌራ፥ አቢሁድ፥ አቢሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፥ ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም።
5
6እነዚህም የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤
7ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ ናዕማን፥ አኪያ፥ ጌራ፥ እነርሱም ተማረኩ። ዖዛንና አሒሑድን ወለደ።
8ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ።
9ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፥
10ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፥ ይዑጽን፥ ሻክያን፥ ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።
11ከሑሺምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ።
12የኤልፍዓልም ልጆች፤ ዔቤር፥ ሚሻም፥ ኦኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ፤
13በሪዓ፥ ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤
14አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት፥
15
16ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔድር፥ ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ፥ የበሪዓ ልጆች፤
17ዝባድያ፥ ሜሱላም፥
18ሕዝቂ፥ ሔቤር፥ ይሽምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ፥ የኤልፍዓል ልጆች፤
19ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ፥
20
21ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች፤
22ይሽጳን፥
23ዔቤር፥ ኤሊኤል፥ ዓብዶን፥ ዝክሪ፥
24
25ሐናን፥ ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ፥ ይፍዴያ፥ ፋኑኤል፥ የሶሴቅ ልጆች፤
26ሸምሽራይ፥
27ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች።
28እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
29የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል፥
30የበኵር ልጁ ዓብዶን፥
31ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ናዳብ፥ ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር በገባዖን ተቀመጡ።
32ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ።
33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ።
34የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።
35የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።
36አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።
37ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁም ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤
38ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሽዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።
39የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት።
40የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኃያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ አምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።