English

ምዕራፍ 26

1በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ በላይ ራብ ሆነ፤ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።
2እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው። ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ።
3በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፤ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።
4ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም አህዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤
5አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።
6ይስሐቅም በጌራራ ተቀመጠ።
7የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት፤ እርሱም። እኅቴ ናት አለ፤ የዚህ ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ እርስዋ ውብ ነበረችና።
8በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ።
9አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ፥ እንዲህም አለው። እነሆ ሚስትህ ናት፤ እንዴትስ እርስዋን። እኅቴ ናት አልህ? ይስሐቅም። በእርስዋ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው አለው።
10አቢሜሌክም አለ። ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ከሕዝብ አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፥ ኃጢአትንም ልታመጣብን ነበር።
11አቢሜሌክም ሕዝቡን ሁሉ። ይህን ሰው ሚስቱንም የሚነካ ሞትን ይሙት ብሎ አዘዘ።
12ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
13ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ፥ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመረ ይበዛ ነበር፤
14የበግና የላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት፤ የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት።
15በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጕድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው አፈርንም ሞሉባቸው።
16አቢሜሌክም ይስሐቅን። ከእኛ ተለይተህ ሂድ፥ ከእኛ ይልቅ እጅግ በርትተሃልና አለው።
17ይስሐቅም ከዚያ ሄደ፥ በጌራራም ሸለቆ ሰፍሮ በዚያ ተቀመጠ።
18ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ቈፍረዋቸው የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፤ አብርሃም ከሞተ በኋላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበሩና፤ አባቱም ይጠራቸው በነበረው ስም ጠራቸው።
19የይስሐቅ ሎሌዎችም በሸለቆው ውስጥ ቈፈሩ፥ በዚያም የሚመነጭ የውኃ ጕድጓድ አገኙ።
20የጌራራ አገር እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር። ውኃው የእኛ ነው ሲሉ ተከራከሩ፤ የዚያችንም ጕድጓድ ስም ኤሴቅ ብሎ ጠራት፥ ለእርስዋ ሲሉ ተጣልተዋልና።
21ሌላ ጕድጓድም ማሱ፥ ስለ እርስዋም ደግሞ ተጣሉ፤ ስምዋንም ስጥና ብሎ ጠራት ።
22ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም ርኆቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል። አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።
23
24ከዚያም ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው። እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤ እባርክሃለሁ፤ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።
25በዚያም መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፥ በዚያም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ።
26አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱም አለቃ ፊኮል ከጌራራ ወደ እርሱ ሄዱ።
27ይስሐቅም። ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል፥ ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል አላቸው።
28
29እነርሱም አሉት። እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን፤ ስለዚህም። በእኛና በአንተ መካከል መሐላ ይሁን፤ እኛ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በደኅናም እንደ ሰደድንህ፥ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን ቃል ኪዳን ከአንተ ጋር እናድርግ አልን፤ አንተ አሁን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረክህ ነህ።
30ይስሐቅም ማዕድ አቀረበላቸው፥ በሉም ጠጡም።
31ማልደውም ተነሡ፥ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ፤ ይስሐቅም አሰናበታቸው፥ ከእርሱም ወጥተው በደኅና ሄዱ።
32በዚያም ቀን የይስሐቅ ሎሌዎች መጡ፥ ስለቈፈሩአትም ጕድጓድ። ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።
33ስምዋንም ሳቤህ ብሎ ጠራት፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው።
34ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
35እነርሱም የይስሐቅንና የርብቃን ልብ ያሳዝኑ ነበር። a