English

ምዕራፍ 136

1እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
3የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
4እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
5ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
6ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
7ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
8ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
9ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
10ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
11እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
12በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
13የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
14እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
15ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
16ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
17ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
18ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
19የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
20የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
21ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
22ለባሪያው ለእስራኤል ርስት፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
23እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
24ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
25ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
26የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።